Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 41:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ስለዚህ አንተን በአገሬ ላይ አስተዳዳሪ አድርጌ እሾምሃለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይታዘዝሃል፤ በሥልጣንም ከእኔ በቀር የሚበልጥህ የለም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝ​ቤም ሁሉ ለቃ​ልህ ይታ​ዘዝ፤ እኔም ከዙ​ፋኔ በቀር ከአ​ንተ የም​በ​ል​ጥ​በት የለም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 አንተ በቤቴ ላይ ተሾምክ ሕዝቤም ሁሉ ለቃልህ ይታዘዝ እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 41:40
16 Cross References  

ከመከራውም ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብጽና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።


በሥራው ብልህ ሰው ትመለከታለህን? በነገሥታት ፊት ያገለግላል፥ በተራ ሰዎችም ፊት ሊያገለግል አይቆምም።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።


ልቤ በስውር ተታልሎ፥ አፌም እጄን ስሞ እንደሆነ፥


ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፥ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ ሳመው፥ እንዲህም አለው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ጌታ ቀብቶህ የለምን?


በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት ያለው ማንም የለም፤ እርሱ ያልሰጠኝ ነገር ቢኖር፥ አንቺን ብቻ ነው፤ ያውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ?”


ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements