ዘፍጥረት 41:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፣ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ከዚያ በኋላ ሰባት የራብ ዓመቶች ይመጣሉ፤ ራብ አገሪቱን በብርቱ ስለሚጐዳት እነዚያ የጥጋብ ዓመቶች ይረሳሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ደግሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመጣል፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ የነበረውንም ጥጋብ ሁሉ ይረሱታል፤ ራብም ምድርን ሁሉ ያጠፋል፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ደግሞ ከዚህ በኍላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል See the chapter |