ዘፍጥረት 38:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፥ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፥ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከርሷ ጋራ አልተኛም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ይሁዳም ዕቃዎቹ የማን እንደ ሆኑ ዐውቆ “ከልጄ ከሴላ ጋር ስላላጋባኋት እርስዋ ከእኔ ይልቅ ትክክለኛ ሆና ተገኘች” አለ፤ ወደ እርስዋም ዳግመኛ አልገባም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ይሁዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕማር እውነተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና” አለ። ትገደል ማለትንም ተወ፤ ደግሞም አላወቃትም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነትኛ ሆነች ልጄን ሴሎምን አልሰጠኍትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም። See the chapter |