Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 38:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይህም በጌታ ፊት ክፉ አድራጎት ሆኖ ስለ ተገኘ፥ እርሱንም ጌታ በሞት ቀሠፈው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድራጎት ሆኖ ስለ ተገኘ፣ እርሱንም እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህን በማድረጉ እግዚአብሔርን ስላሳዘነ እግዚአብሔር እርሱንም በሞት ቀሠፈው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይህም ሥራው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ክፉ ሆነ​በት፤ እን​ዲህ አድ​ር​ጎ​አ​ልና እር​ሱ​ንም ደግሞ ቀሠ​ፈው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፋ ሆነበት፥ እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 38:10
13 Cross References  

የይሁዳም ልጆች፥ ዔር፥ ኦውናን፥ ሴላ፥ ፋሬስ፥ ዛራሕ፥ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፥ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል።


የይሁዳ ልጆች ዔርና አውናን ናቸው፤ ዔርና አውናንም በከነዓን ምድር ሞቱ።


ሕዝቡም ስለ ደረሰባቸው መከራ በጌታ ላይ አጉረመረሙ፤ ጌታም ሰምቶ እጅግ ተቈጣ፤ የጌታም እሳት በመካከላቸው ነደደ፥ የሰፈሩንም ዳር በላ።


የጌታ መልእክተኛ ሐጌ በጌታ መልእክት ሕዝቡን፦ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ይላል ጌታ” ብሎ ተናገረ።


ሆኖም በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ እንዲህ ብዬ ላክሁባችሁ፦ ‘እባካችሁ፥ እንደዚህ ያለ የጠላሁትን ርኩስ ነገር አታድርጉ።’


ጌታ ይህንን አይቶ እንዳያዝንብህ፥ ቁጣውንም ከእርሱ ላይ እንዳያነሣ።


ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።


ከዚህም ነገር የተነሣ እግዚአብሔር ተቈጣ፥ እስራኤልንም ቀሠፈ።


የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፥ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ ጌታን አላስደሰተውም ነበር።


በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”


ሰውስ በሰው ቢበድል እግዚአብሔር ይታደገዋል፤ ሰው ግን ጌታን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” እነርሱ ግን ጌታ ሊገድላቸው ወድዷልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።


ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታ አምላኬ ሆይ! ስለምን በዚህች ባሏ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርሷ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጇ እንዲሞት አደረግህ?” ሲል ጸለየ።


የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴዋ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። የይሁዳም የበኩር ልጅ ዔር በጌታ ፊት ክፉ ነበረ፤ እርሱም ገደለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements