ዘፍጥረት 32:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ከዚያ ሰውየው፦ “የንጋት ጎህ ሊቀድ ነውና ልቀቀኝ” አለው። እርሱም፦ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 በዚያ ጊዜ ሰውየው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለ ሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ። ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 እንዲህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድዶአልና ልቀቀኝ።” እርሱም “ከአልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው። See the chapter |