Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 31:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 እኔ ወደ አንተ ይህን ክምር እንዳላልፍ፥ አንተም ለክፋት ወደ እኔ ይህን ክምርና ይህን ሐውልት እንዳታልፍ፥ ይህ ክምር እና ይህ ሐውልት ምስክር ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ይህን ክምር ድንጋይ ዐልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት ዐልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፣ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 እኔ አንተን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልል እንደማላልፍ፥ አንተም እኔን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልልና ይህን የመታሰቢያ ሐውልት እንደማታልፍ፥ ይህ የድንጋይ ቊልልና ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ምስክሮች ናቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 እኔ ወደ አንተ በክ​ፋት ባልፍ ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር፥ ይህ​ችም ሐው​ልት በክፉ ነገር ትከ​ተ​ለኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 እኔ ወደ አንተ ይህችን ክምር እንዳላልፍ አንተም ለክፋት ወደ እኔ ይህችን ክምርና ይህችን ሐውልት እንዳታልፋት ይህች ክምር ምስክር ናት ይህችም ሐውልት ምስክር ናት።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 31:52
5 Cross References  

ላባም፥ “ይህ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለ። ስለዚህም ገለዓድ ብሎ ሰየማት፥


ላባም ያዕቆብን አለው፥ “በእኔና በአንተ መካከል ይህ ክምር፥ ያቆምኩት ሐውልትም እነሆ፥


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ፥ የአባታቸውም አምላክ፥ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በአንድነትም መሥዋዕታችን ጌታን እንድናገለግል፥ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻንን፦ “በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም” እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements