ዘፍጥረት 31:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 ራሔልም ተራፊምን ወስዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች፥ በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ፥ አንዳችም አላገኘም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም34 ራሔል የጣዖታቱን ምስል ከግመሏ ኮርቻ ሥር ሸሽጋ፣ በላዩ ተቀምጣበት ነበር፤ ላባም ድንኳኑን አንድ በአንድ በርብሮ ምንም ሊያገኝ አልቻለም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 ራሔል ግን ጣዖቶቹን ወስዳ በግመሉ ኮርቻ ሥር በመሰወር በላያቸው ላይ ተቀምጣባቸው ነበር፤ ላባ በድንኳኑ ውስጥ ያለውን ጓዝ ሁሉ በርብሮ ምንም ነገር አላገኘም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 ራሔልም የአባቷን ጣዖቶች ወስዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች፤ በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ፤ አንዳችም አላገኘም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 ራሔልም ተራፊምን ወሰዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ አንዳችም አላገኘም። See the chapter |