Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባርያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆንውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ልያም ልጅ መውለድ ማቆሟን እንደ ተረዳች፣ አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንድትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ልያም መውለድ እንዳቆመች በተገነዘበች ጊዜ አገልጋይዋን ዚልፋን እንደ ሚስት አድርጋ ለያዕቆብ ሰጠችው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ልያም መው​ለ​ድን እን​ዳ​ቆ​መች በአ​የች ጊዜ አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን ዘለ​ፋን ወሰ​ደች፤ ሚስት ትሆ​ነ​ውም ዘንድ ለያ​ዕ​ቆብ ሰጠ​ችው፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባሪያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆንውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:9
8 Cross References  

ባርያዋን ባላንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ለእርሱ ሰጠችው፥ ያዕቆብም ደረሰባት።


እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።


ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፥ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።


አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባርያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።


ራሔልም፦ ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች፥ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።


የልያ ባርያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች።


ላባም ለልጁ ለልያ ባርያይቱን ዘለፋን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት።


እነዚህ ዐሥራ ስድስቱ ላባ ለልጁ ለልያ በሞግዚትነት ከሰጣት ከዚልፋ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements