Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ “ወደ እኔ ትገባለህ፥ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና።” በዚያችም ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኛ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚያች ምሽት ያዕቆብ ከዕርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለ ተከራየሁህ የዛሬው ዐዳርህ ከእኔ ጋራ ነው” አለችው፤ ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከርሷ ጋራ ዐደረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በዚያን ምሽት ያዕቆብ ከዱር ሲመለስ፥ ልያ ከቤት ወደ እርሱ ወጥታ “በልጄ እንኮይ ስለ ገዛሁህ ዛሬ ሌሊት የምታድረው ከእኔ ጋር ነው” አለችው፤ ስለዚህ በዚያን ሌሊት ከእርስዋ ጋር ዐደረ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ያዕ​ቆ​ብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ እን​ዲ​ህም አለ​ችው፥ “እኔ ዘንድ ታድ​ራ​ለህ፤ በልጄ እን​ኮይ በእ​ር​ግጥ ተስ​ማ​ም​ቼ​ሃ​ለ​ሁና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ያዕቆብ ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ ወደ እኔ ትገባለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና። በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር ተኛ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:16
3 Cross References  

ሮቤልም ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፥ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት። ራሔልም ልያን፦


“የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች።


እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements