ዘፍጥረት 30:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 “የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ልያም፣ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ?” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለ ልጅሽ እንኮይ ዛሬ ከአንቺ ጋራ ይደር” አለቻት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ልያም “ባሌን የነጠቅሽኝ አንሶሽ፥ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣልኝን እንኮይ መቀማት ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “ከልጅሽ እንኮይ ስጪኝና ዛሬ ሌሊት ያዕቆብ ካንቺ ጋር ይደር” አለቻት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ልያም፥ “ባሌን መውሰድሽ አይበቃሽምን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠቻትም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ራሔልም ልያን፦ የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ አለቻት። እርስዋም፦ ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊአለሽን? አለቻት። ራሔልም፦ እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ አለች። See the chapter |