Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሮቤልም ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፥ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት። ራሔልም ልያን፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስንዴ በሚታጨድበት ወቅት፣ ሮቤል ወደ ሜዳ ወጣ፤ እንኮይም አግኝቶ ለእናቱ ለልያ አመጣላት። ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔል ልያን “እባክሽ ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሮቤል ስንዴ በሚ​ታ​ጨ​ድ​በት ወራት ወጣ፤ በእ​ር​ሻም እን​ኮይ አገኘ፥ ለእ​ናቱ ለል​ያም አመ​ጣ​ላት። ራሔ​ልም ልያን፥ “የል​ጅ​ሽን እን​ኮይ ስጪኝ” አለ​ቻት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሮቤልም ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፥ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:14
5 Cross References  

ትርንጎዎች መዓዛን ሰጡ፥ መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥ አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፥ ውዴ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።


ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ እርቦኛልና!” አለው፤ (ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።)


“የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች።


ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ “ወደ እኔ ትገባለህ፥ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና።” በዚያችም ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኛ።


ከስምዖንም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሳኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements