ዘፍጥረት 29:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ደገመኝ አለች፥ ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 እንደ ገናም ፀንሳ ወለደች፤ እርሷም “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰምቶ ይህን ልጅ በድጋሚ ሰጠኝ” አለች። ከዚያም የተነሣ ስምዖን ብላ ጠራችው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ስምዖን አለችው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ልያም ዳግመኛ ፀነሰች፤ ሁለተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት፤ “እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ጨመረልኝ” አለች፤ ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች፤ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ስማ ይህን ደገመኝ አለች ስምዖን ብላ ጠራችው See the chapter |