ዘፍጥረት 29:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በሜዳውም እነሆ ጉድጓድን አየ፥ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፥ ከዚያ ጉድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፥ በጉድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እዚያም በአንድ ሜዳ ላይ ሦስት የበግ መንጋዎች ተኝተው በነበሩበት አጠገብ የውሃ ጕድጓድ አየ። የበግ መንጋዎቹ የሚጠጡት ከዚሁ ጕድጓድ ሲሆን፣ የጕድጓዱም አፍ ትልቅ የድንጋይ መክደኛ ነበረው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጒድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጒድጓዱ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጒድጓድ ነበር፤ ጒድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በተመለከተም ጊዜ በሜዳው እነሆ ጕድጓድን አየ፤ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያች ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓድዋም አፍ ታላቅ ድንጋይ ነበረች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 በሜዳውም እነሆ ጕድጓድም አየ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በለዩ ተመስገው ነበር ከዚያ ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። See the chapter |