Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 29:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ላባም፦ “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል፥ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ላባም መልሶ፣ “ለሌላ ሰው ከምድራት ላንተ ብድራት ይሻላል፤ እዚሁ ዐብረኸኝ ተቀመጥ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ላባም “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ላባም፥ “ለሌላ ሰው ከም​ሰ​ጣት ይልቅ ለማ​ው​ቅህ ለዘ​መዴ ለአ​ንተ ብሰ​ጣት ይሻ​ላል፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ላባም፦ ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል ከእኔ ጋር ተቀመጥ አለ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 29:19
6 Cross References  

እኔም፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፤ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፤ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፤ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


ያዕቆብም ራሔልን ወደደ፥ እንዲህም አለ፦ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ።”


ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፥ እርሷንም ይወድዳት ስለ ነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።


ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ በዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements