Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 27:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከመሞቴ በፊት እንድመርቅህ የምወድደውን ዐይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ አብላኝ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሠርተህ አምጣልኝ፤ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሳል​ሞ​ትም ነፍሴ እን​ድ​ት​ባ​ር​ክህ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ደው መብል አዘ​ጋ​ጅ​ተህ እበላ ዘንድ አም​ጣ​ልኝ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅትህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 27:4
23 Cross References  

ይስሐቅ ስለ መጪው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።


ዮሴፍም ለአባቱ፦ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው” አለ። እርሱም፦ “እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ” አለ።


እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፥ አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም፥ እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።


እርሱም፦ “ከልጄ አደን እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አቅርብልኝ” አለ። አቀረበለትም፥ በላም፥ የወይን ጠጅ አመጣለት፥ እርሱም ጠጣ።


እየባረካቸውም ከእነርሱ ተለየ፤ ወደ ሰማይም ዐረገ።


ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፦ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን በእስራኤል ላሉት ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት እንዲሆን ተሾሞአል፤


ኢያሱም ባረካቸው፥ እንዲሄዱም አሰናበታቸው፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።


ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው።


‘አደን አድነህ አምጣልኝ፥ ሳልሞትም በልቼ በጌታ ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል ሥራልኝ፤’ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ።


ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፥


እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አገባ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ይነሣ፥ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ” አለው።


ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥


እርሱም አላወቀውም ነበር፥ እጆቹ እንደ ወንድሙ እንደ ዔሳው እጆች ጠጉራም ነበሩና፥ ስለዚህም ባረከው።


ርብቃንም መረቁአትና፦ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፥ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ” አሉአት።


እንዲህም ሲል ባረከውም፦ አብራም ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው፥ ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ፥


ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ሲነግር ትሰማ ነበር። ዔሳውም አደን አድኖ ሊያመጣ ወደ ምድረ በዳ ሄደ።


ወደ መንጋ ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፥ እነርሱንም ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፥


ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች።


የሠራችውን ጣፋጭ መብልና እንጀራውን ለልጇ ለያዕቆብ በእጁ ሰጠችው።


ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements