Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 27:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ዔሳውም አባቱን አለው፦ “አባቴ ሆይ፥ በረከትህ አንዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ።” ዔሳውም ቃሉን አንሥቶ አለቀሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ዔሳውም አባቱን፣ “አባቴ ሆይ፤ ምርቃትህ ይህችው ብቻ ናትን? እባክህ አባቴ፣ እኔንም መርቀኝ” አለው፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ዔሳውም “አባቴ ሆይ! ምርቃትህ አንዲት ብቻ ናትን? እባክህ እኔንም መርቀኝ” እያለ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ዔሳ​ውም አባ​ቱን ይስ​ሐ​ቅን አለው፥ “አባቴ ሆይ፥ በረ​ከ​ትህ አን​ዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ከኝ።” ዔሳ​ውም ጮሆ አለ​ቀሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ዔሳውም አባቱን አለው፦ አባቴ ሆይ እኔንም ደግሞ ባርከኝ። ዔሳውም ቃሉን አንሥቶ አለቀሰ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 27:38
8 Cross References  

በኋላ እንኳን በረከቱን ለመውረስ ቢፈልግም እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ ቢፈልግም እንኳን ለንስሓ ስፍራ አላገኘምና።


ዔሳውም የአባቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ እጅግም መራራ ጩኸት ጮኸ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ” አለው።


እነሆ፥ አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፥ እናንተ ግን ከልባችሁ ኀዘን የተነሣ ትጮኻላችሁ፥ መንፈሳችሁም ስለ ተሰበረ ወዮ ትላላችሁ።


እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፥ አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም፥ እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፥ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፥ ብኩርናዬን ወሰደ፥ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?” አለ።


መልእክተኞቹም ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው ይህን ለሕዝቡ በተናገሩ ጊዜ፥ ሕዝቡ ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements