ዘፍጥረት 27:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 እርሱም እንዲህ አለ፦ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፥ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፥ ብኩርናዬን ወሰደ፥ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?” አለ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ዔሳውም፣ “ይህ ሰው ያዕቆብ መባሉ ትክክል አይደለምን? እኔን ሲያታልለኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ” አለ። ቀጥሎም፣ “ታዲያ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለም?” ብሎ ጠየቀ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ዔሳውም “እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኲርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ፥ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለምን?” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ዔሳውም አለ፥ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደ፤ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ።” ዔሳውም አባቱን አለው፥ “ደግሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 እርሱም አለ፦ በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ ብኵርናዬን ወሰደ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን? አለ። See the chapter |