Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 27:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አገባ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ይነሣ፥ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እርሱም ደግሞ ጣፋጭ ምግብ በማዘጋጀት ለአባቱ አቅርቦ፣ “አባቴ ሆይ፤ እንድትመርቀኝ፣ እስኪ ቀና በልና ካደንሁት ብላ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና “አባቴ ሆይ፥ እንድትመርቀኝ፥ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እር​ሱም ደግሞ መብል አዘ​ጋጀ፥ ለአ​ባ​ቱም አመጣ፤ አባ​ቱ​ንም፥ “አባቴ ተነሥ፤ ነፍ​ስ​ህም ትባ​ር​ከኝ ዘንድ ልጅህ ከአ​ደ​ነው ብላ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ ለአባቱም አገባ አባቱንም፦ አባቴ ይነሣ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ አለው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 27:31
4 Cross References  

ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።”


ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።”


ይስሐቅም ያዕቆብን ባርኮ ከፈጸመ በኋላ፥ ያዕቆብም ከአባቱ ከይስሐቅ ፊት ከወጣ በኋላ፥ ወዲያው በዚያው ጊዜ ዔሳው ከአደኑ መጥቶ ገባ።


ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements