ዘፍጥረት 27:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ይስሐቅም ልጁን፦ “ልጄ ሆይ፥ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው?” አለው። እርሱም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው” አለ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ይሥሐቅ ልጁን፣ “ልጄ ሆይ፤ ከመቼው ቀንቶህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም፣ “እግዚአብሔር አምላክህ አሳካልኝ” ብሎ መለሰለት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ይስሐቅም “ልጄ ሆይ፥ እንዴት በቶሎ ልታገኝ ቻልክ?” አለው። ያዕቆብም “አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልኩ” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ይስሐቅም ልጁን፥ “ልጄ ሆይ፥ ፈጥነህ ያገኘኸው ይህ ምንድን ነው?” አለው። እርሱም፥ “አምላክህ እግዚአብሔር በፊቴ የሰጠኝ ነው” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ። See the chapter |