ዘፍጥረት 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት፥ እርሱም፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፥ እርሷ ውብ ነበረችና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለ ሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የዚህ ስፍራ ሰዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ እርስዋም ውብ ነበረችና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት እርሱም፦ እኅቴ ናት አለ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና እርስዋ ውብ ነበረችና። See the chapter |