Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 26:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ማልደውም ተነሡ፥ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ፥ ይስሐቅም አሰናበታቸው፥ ከእርሱም ወጥተው በሰላም ሄዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በማግስቱም በማለዳ ተነሥተው፣ በመካከላቸው መሐላ ፈጸሙ። ይሥሐቅም አሰናበታቸው፤ እነርሱም በሰላም ሄዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተማ​ማሉ፤ ይስ​ሐ​ቅም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ከእ​ር​ሱም በደ​ኅና ሄዱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ማልደውም ተነሡ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ ይስሐቅም አሰናበታቸው ከእርሱም ወጥተው በደኅና ሄዱ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 26:31
16 Cross References  

ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት የክርክር ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤


ዳዊትም፥ “ታዲያ ወራሪው ሠራዊት ወዳለበት መርተህ ትወስደኛለህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እንደማትገድለኝ ወይም ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ እነዚህ ወራሪዎች ወዳሉበት አደርስሃለሁ” አለው።


አሁንም ና፥ አንተና እኔ ቃል ኪዳን እንጋባ፥ በእኔና በአንተ መካከልም ምስክር ይሁን።”


ያዕቆብም፥ “እስኪ በቅድሚያ ማልልኝ” አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኲርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።


ዳዊት ግን፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው ጌታን! በነፍስህ እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።


ሳኦል፥ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት፥ እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አስምሎ ስለ ነበር፥ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም።


ጠዋት በማለዳ ላባ ተነሥቶ የልጅ ልጆቹን እና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም፥ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።


በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ።


አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፥ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።”


አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፥ እርሷም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።


“ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባርያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፥ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፦ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።


አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፥


አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፥ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።


በዚያም ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጡ፥ ስለ ቈፈሩአትም ጉድጓድ፦ “ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements