Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፥ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ፣ እነሆ፤ ከአብርሃም ወንድም ከናኮርና ከሚስቱ ከሚልካ የተወለደው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት በቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እን​ደ​ዚህ በልቡ ያሰ​በ​ውን መና​ገ​ሩን ሳይ​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፦ የአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም የና​ኮር ሚስት የሚ​ልካ ልጅ የባ​ቱ​ኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም በጫ​ን​ቃዋ ተሸ​ክማ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፤ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:15
22 Cross References  

አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፥ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፥ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፥ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።


እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።


“እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም፥ እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች፥ ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ ‘እስኪ አጠጪኝ’ አልኋት።


የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥


አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ስእለት ይቀርባል።


ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥ ሰላምን እሻ ተከተላትም።


የምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፥ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውሀውን ገንዳ ሞሉ።


በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፥ የቃረመችውንም ወቃችው፥ ዐሥር ኪሎ ያህልም ገብስ ሆነ።


ሞአባዊቱም ሩት ናዖሚንን፦ “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው ተከትዬ እህል ለመቃረም ወደ እርሻ ልሂድ” አለቻት። እርሷም፦ “ልጄ ሆይ፥ ሂጂ” አለቻት።


እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረሰች፥ እርሷ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና።


አለችውም፦ “እኔ ሚልካ ለናኮር የወለደችው የባቱኤል ልጅ ነኝ።


የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፥ ሐራንም ሎጥን ወለደ።


የቤትዋንም ሰዎች አካሄድ በደኅና ትመለከታለች፥ የሀኬትንም እንጀራ አትበላም።


አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፥ እርሷም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።


ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርሷም አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርሷ ለባርያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፥ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”


ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፥ እርሷም በመስጴጦምያ የሚኖሩ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት።


በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው።


“የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፦ “እናውቀዋለን” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements