Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 23:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን ይስጠኝ፥ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንዲሰጠኝ አድርጉልኝ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይኸውም በዕርሻው ድንበር ላይ ያለችውን መክፈላ የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ነው፤ በመካከላችሁም የመቃብር ቦታ እንድትሆነኝ በሙሉ ዋጋ እንዲሸጥልኝ ለምኑልኝ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በእርሻው ድንበር ላይ ያለችውን ማክፌላ የተባለችውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻ እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፤ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በእ​ር​ሻው ዳር ያለ​ች​ውን ድርብ ክፍል ያላ​ትን ዋሻ​ውን ይስ​ጠኝ፤ መቃ​ብሩ የእኔ ርስት እን​ዲ​ሆን በሚ​ገ​ባው ዋጋ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይስ​ጠኝ፤ ከእ​ር​ሱም እገ​ዛ​ለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን በሙሉ ዋጋ በመካከላችሁ ይስጠኝ፥ መቃብሩ የእኔ ርስት እንዲሆን።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 23:9
10 Cross References  

እርስ በእርሳችሁ ከመዋደድ በቀር የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሟልና።


ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ።


“እኔ በመካከላችሁ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ፥ በእናንተ ዘንድ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፥ ሬሳዬንም ከፊቴ አርቄ ልቅበር።”


እንዲህም አላቸው፦ “ሬሳዬን ከፊቴ አርቄ እንድቀብር ከወደዳችሁስ ስሙኝ፥ ከሰዓር ልጅ ከኤፍሮንም ለምኑልኝ፥


ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፥ የኬጢ ሰው ኤፍሮንም የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦


የእርሻው ቦታ አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው ነው፤ ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ ሣራ ጋር ተቀበረ።


እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ “እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ፥ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፥


ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፥ እርሷም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።


ዳዊትም ኦርናን፦ “በላዩ ለጌታ መሠዊያ እንድሠራ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ ሙሉ ዋጋ ልክፈልና ስጠኝ፤ መቅሰፍቱም ከሕዝቡ ይከለከላል” አለው።


ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፦ “አይደለም፥ ነገር ግን የአንተ የሆነውን ለጌታ አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements