Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በማግስቱም ጧት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይሥሐቅን ይዞ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጕዞውን ጀመረ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አብረሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፥ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሕቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 22:3
16 Cross References  

ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።


በአሕዛብ መካከል ወንጌሉን እንድሰብክ፥ ልጁን በእኔ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፤


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፥ እርሷም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።


አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።


አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴትም እንደሚሄድም ሳያውቅ ሄደ።


እግዚአብሔርም፥ “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፥ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋልኝ” አለው።


በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ።


ቃሌን ሰምተሃልና፥ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ።”


ኢያሱም ማልዶ በጠዋት ተነሣ፥ ሕዝቡንም ሰበሰበ፤ እርሱም ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።


በማግስቱም ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements