Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 21:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በቤርሳቤህም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በቤርሳቤህ የስምምነት ውል ካደረጉ በኋላ፣ አቢሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ተመለሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይህን ስምምነት በቤርሳቤህ ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሠራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገ​ብም ቃል ኪዳ​ንን አደ​ረጉ። አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዞት፥ የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮ​ልም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ተመ​ለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በቤርሳቤህም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነስተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 21:32
12 Cross References  

ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም ጌታ በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው።


እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ቅርብ ቢሆን በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብጽም እንዳይመለስ” ብሏልና።


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ፥ የአባታቸውም አምላክ፥ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


በግና ላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፥ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።


በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።


አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፥ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።


አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።


ፈትሮሳውያን፥ ከስሉሃውያን (ከእነርሱም ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው)፥ እና የካፍቶር ሕዝቦች ናቸው።


ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው፥ ከዚያ ሁለቱ ተማምለዋልና።


አብርሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍን ተከለ፥ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።


አሁንም ና፥ አንተና እኔ ቃል ኪዳን እንጋባ፥ በእኔና በአንተ መካከልም ምስክር ይሁን።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements