ዘፍጥረት 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አቢሜሌክም በነገታው ማልዶ ተነሣ፥ ባለሟሎቹንም ሁሉ ጠርቶ የሆነውን ነገር ሁሉ ነገራቸው፥ ሰዎቹም እጅግ ደነገጡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በማግስቱም ማለዳ፣ አቢሜሌክ ሹማምቱን ሁሉ ጠርቶ፣ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፤ እነርሱም ታላቅ ፍርሀት ዐደረባቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በማግስቱ ጠዋት በማለዳ አቤሜሌክ ባለሟሎቹን ጠርቶ የሆነውን ነገር ሁሉ በተረከላቸው ጊዜ ደነገጡ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አቤሜሌክም በጥዋት ተነሣ፤ ብላቴኖቹንም ሁሉ ጠራ፤ ይህንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ፤ ቤተ ሰዎቹም ሁሉ እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አቢሜሌክም በነገታው ማለደ፥ ባሪያዎቹንም ሁሉ ጠራ ይህንንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ ስዎቹም እጅግ ፈሩ። See the chapter |