Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 20:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ ‘በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።’”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር አዝዞኝ ከአባቴ ቤት ወጥቼ በየአገሩ ስዞር፣ ‘ለእኔ ያለሽን ፍቅር በዚህ ግለጭልኝ፤ በየደረስንበት ስፍራ ሁሉ “እርሱ ወንድሜ ነው” በዪ’ ብያት ነበር።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ቤት ባወ​ጣኝ ጊዜ አል​ኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድ​ር​ጊ​ልኝ፤ በገ​ባ​ን​በት ሀገር ሁሉ ወን​ድሜ ነው በዪ።’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኍት በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፤ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለእኔ ተናገሪ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 20:13
10 Cross References  

እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።


አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ።


አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴትም እንደሚሄድም ሳያውቅ ሄደ።


ጴጥሮስም “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው፤ አንቺንም ያወጡሻል፤” አላት።


ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም።


ሳኦል እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለእኔ ስለ ተቆረቆራችሁ ጌታ ይባርካችሁ፤


‘እኅቴ ናት’ ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርሷም ደግሞ ራስዋ፥ ‘ወንድሜ ነው’ ብላኛለች፥ ይህንን በቅን ልብ እና በንጹሕ ኅሊና ነው ያደረግሁት”።


እርሷም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት፥ የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት፥ ለእኔም ሚስት ሆነች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements