Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፥ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፥ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነሆ፤ ወንድ የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ። እነርሱን ላውጣላችሁና የፈለጋችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን አንዳች ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ገብተዋልና።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነሆ፥ ሁለት ያላገቡ ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ወደ እናንተ ላምጣላችሁና በእነርሱ ላይ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉ፤ በእነዚህ ሰዎች ግን ምንም ነገር አታድርጉ፤ እነርሱ የእኔ እንግዶች ስለ ሆኑ ልጠነቀቅላቸው ይገባኛል።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነሆ፥ ወን​ድን ያላ​ወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነ​ር​ሱን ላው​ጣ​ላ​ችሁ፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁም አድ​ር​ጉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታ​ድ​ርጉ፤ እነ​ርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብ​ተ​ዋ​ልና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነሆ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ እነርሱን ላውጣላች እንደ ወደዳችሁም አደርጓቸው በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 19:8
12 Cross References  

እነሆ ድንግል የሆነች ልጄና የሰውየው ቊባት አሉ፤ እነርሱን አሁኑኑ ላውጣላችሁና አስነውሯቸው፤ ያሻችሁንም አድርጉባቸው፤ በዚህ ሰው ላይ ግን እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙበት።”


“መልካም ነገር እንዲመጣ ለምን ክፉ አናደርግም?” ይላሉ ብለው እንደሚያሙን አይደለም፤ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።


እጅግ ስለ ፈሩ የሚናገረውን አያውቅም ነበር።


እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?


የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።


አሮንም እንዲህ አለ፦ “የጌታዬ ቁጣ አይንደድ፤ ይህ ሕዝብ ክፋ እንደሆነ አንተ ታውቃለህ።


በዚህን ጊዜ ሮቤል አባቱን፥ “መልሼ ባላመጣው፥ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው፤ ኀላፊነቱን ለእኔ ተውልኝ፤ እኔው መልሼ አመጣዋለሁ” አለው።


ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት።


እንዲህም አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፥


የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።


ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ክፉንም የሚዘልፍ ኃፍረት ይገጥመዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements