Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 18:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህን? ከተማይቱንስ በእርሷ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ዐምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ ዐምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን ይቅር አትልምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አምሳ ጻድ​ቃን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠ​ፋ​ለ​ህን? ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንስ በእ​ር​ስዋ ስለ​ሚ​ገኙ አምሳ ጻድ​ቃን አት​ም​ር​ምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 18:24
8 Cross References  

በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፤ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር።


እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።


ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል፤” አለኝ።


አብርሃምም ቀረበ ዓለም፦ “በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን?


ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”


ክፋትህ እንደ አንተ ያለውን ሰው ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements