ዘፍጥረት 14:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፥ የአሕዛብን ንጉሥ ቲድዓልን፥ የሰናዖርን ንጉሥ አምራፌልን፥ የእላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት አምስቱ ነገሥታት በእነዚህ በአራቱ ላይ ወጡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እነዚህ ዐምስቱ፣ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉሥ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፣ በእነዚህ በአራቱ ላይ ዘመቱባቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 የተዋጉትም ከዔላም፥ ከጎይም፥ ከባቢሎንና ከኤላሳር ነገሥታት ጋር ነበር፤ አምስቱ ነገሥታት ከአራቱ ነገሥታት ጋር የተዋጉት በዚህ ዐይነት ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከኤላም ንጉሥ ከኮሎዶጎሞር፥ ከአሕዛብ ንጉሥ ከቴሮጋል፥ ከሰናዖር ንጉሥ ከአሜሮፌል፥ ከእላሳር ንጉሥ ከአርዮክ ጋር ተጋጠሙ። እነዚህ አራቱ ነገሥታት ከአምስቱ ነገሥታት ጋር ተዋጉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፤ የአሕዛብን ንጉሥ ቲድዓልን፤ የሰናዖርን ንጉሥ አምራፌልን፥ የእላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት አምስቱ ነገሥታት በእነዚህ በአራቱ ላይ ወጡ። See the chapter |