ዘፍጥረት 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የባሉጥ ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፥ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አብራም ትልቁ የሞሬ ዛፍ እስከሚገኝበት እስከ ሴኬም ድረስ በምድሪቱ ዘልቆ ሄደ። በዚያ ጊዜ ከነዓናውያን በዚሁ ምድር ይኖሩ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አብራም በሴኬም ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ ወደ ሞሬ ዛፍ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ፤ በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚያች ምድር ይኖሩ ነበረ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። See the chapter |