ዘፍጥረት 11:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን ተባለ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እግዚአብሔር በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በዚያ እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለ ደበላለቀና እነርሱን በዓለም ዙሪያ ስለ በተናቸው የከተማውም ስም “ባቢሎን” ተባለ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። See the chapter |