ዘፍጥረት 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እግዚአብሔርም ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ከሰማይ በታች ያለው ውኃም በመጠራቀሚያው ተሰበሰበ፤ የብሱም ተገለጠ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እግዚአብሔርም፤ ከሰማይ በታች ያለዉ ውኂ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። See the chapter |