ዘፍጥረት 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” ብሎ ሰየመው፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠራቀሚያውንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። See the chapter |