ገላትያ 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በሥጋ መልካም ሆነው መታየት የሚፈልጉ ሁሉ እንድትገረዙ አስገደዱአችሁ፤ ይህን ያደረጉት ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ውጫዊ በሆነ ነገር ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ትገረዙ ዘንድ ሊያስገድዷችሁ ይጥራሉ፤ ይህንም የሚያደርጉት ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 እንድትገረዙ የሚያስገድዱአችሁ በውጭ መልካም መስለው ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። ይህን የሚያደርጉትም በክርስቶስ መስቀል ምክንያት ስደት እንዳይደርስባቸው ብለው ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ለሰው ፊት ሊያደሉ የሚወዱ እነዚያ እንድትገዘሩ ያስገድዱአችኋል፤ ነገር ግን የክርስቶስን መስቀል እንዳትከተሉ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሉአችሁ፥ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው። See the chapter |