ገላትያ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችሁ ይልቁንም በእግዚአብሔር ታውቃችሁ፥ እንደገና ወደ ደካማና ወደ ተናቀ የመጀመሪያ ትምህርቶች ዳግም ልትገዙላቸው ፈልጋችሁ እንዴት ትመለሳላችሁ? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችሁታል፤ ይልቁን ደግሞ በእግዚአብሔር ታውቃችኋል። ታዲያ እንደ ገና ወደ ደካማና ወደማይጠቅም ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? ዳግም በርሱ በባርነት ለመጠመድ ትፈልጋላችሁን? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችኋል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር እናንተን ዐውቋችኋል፤ ታዲያ፥ ወደ እነዚያ ወደ ደካሞችና ወደማይረቡት የዓለም ሥርዓቶች እንዴት ተመለሳችሁ? እንዴትስ እንደገና የእነርሱ ባሪያዎች ለመሆን ትፈልጋላችሁ? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ዛሬ ግን እግዚአብሔርን ዐወቃችሁት፤ ይልቁንም እርሱ ዐወቃችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደዚያ ወደ ደካማው፥ ወደ ድሀው ወደዚህ ዓለም ጣዖት ተመልሳችሁ፥ ትገዙላቸው ዘንድ እንዴት ፈጠራን ትሻላችሁ? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን? See the chapter |