Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ገላትያ 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባርያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በእግዚአብሔር በኩል ወራሽ ነህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ስለ ሆንህ፣ እግዚአብሔር ወራሽ አድርጎሃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅ ከሆንክም የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ኪ​ያስ እና​ንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ልጆች ከሆ​ና​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ናችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።

See the chapter Copy




ገላትያ 4:7
19 Cross References  

የክርስቶስ ከሆናችሁ ስለዚህ የአብርሃም ዘር ናችሁ፥ በተስፋውም ቃል መሠረት ወራሾች ናችሁ።


በክርስቶስ ኢየሱስ ባላችሁ እምነት ሁላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! የነጻይቱ ልጆች ነን እንጂ የባርያይቱ አይደለንም።


ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥ እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።


ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፥ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች።


የያዕቆብ ድርሻ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙ የሠራዊት ጌታ ነው።


ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ጌታ የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣ ፈንታዬንም የምታጸና አንተ ነህ።


“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements