ገላትያ 4:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ስለዚህ አጋር በዓረብ አገር ያለችው ሲና ተራራ ናት፤ አሁን ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 እንግዲህ አጋር በዐረብ አገር ያለችው የሲናን ተራራ በመወከል አሁን ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፤ ከልጇ ጋራ በባርነት ናትና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 አጋር በዐረብ አገር ለሚገኘው ለሲና ተራራ ምሳሌ ነበረች፤ ስለዚህ ከአሁኒቱ ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ እርስዋ ከነልጆችዋ በባርነት የምትገኝ ናት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አጋርም በዐረብ ሀገር ያለች ደብረ ሲና ናት፤ ከዛሬዪቱ ኢየሩሳሌም ጋር ትነጻጸራለች፤ ከልጆችዋ ጋርም ትገዛለች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። See the chapter |