ገላትያ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ሕግን በመጠበቅ የሚተማመኑ ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏልና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ትእዛዞች ሁሉ ጸንቶ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ “ሕግን በመፈጸም እንጸድቃለን” የሚሉ ሁሉ የተረገሙ ናቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና። See the chapter |