ገላትያ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 አንዳንድ ሰዎች ከያዕቆብ ዘንድ ከመምጣታቸው በፊት ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበር፤ እነሱ በመጡ ጊዜ ግን የተገረዙትን ፈርቶ ወደ ኋላ አፈገፈገ፥ ራሱንም ለየ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 አንዳንድ ሰዎች ከያዕቆብ ዘንድ ከመምጣታቸው በፊት፣ ከአሕዛብ ጋራ ይበላ ነበር፤ እነርሱ በመጡ ጊዜ ግን፣ የተገረዙትን ወገኖች ፈርቶ ከአሕዛብ ራሱን በመለየት ገሸሽ ማለት ጀመረ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ያዕቆብ የላካቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ አንጾኪያ ከመምጣታቸው በፊት ከአሕዛብ መካከል ከአመኑት ጋር አብሮ ይበላ ነበር፤ እነርሱ ከመጡ በኋላ ግን “ከአሕዛብ ወገን ያመኑት መገረዝ አለባቸው” የሚሉትን ቡድኖች በመፍራት ወደ ኋላ አፈግፍጎ ከአሕዛብ ተለየ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ሰዎች ከያዕቆብ ዘንድ ከመምጣታቸው በፊት፥ ከአረማውያን ጋር ይበላ ነበርና፥ በመጡ ጊዜ ግን ተለያቸው፤ ከአይሁድ ወገን የሆኑትን ፈርቶአልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ። See the chapter |