ዕዝራ 8:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ንጉሡ፥ አማካሪዎቹ፥ ባለሥልጣናቱ በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ፤ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን የብሩንና፥ የወርቁን፥ የዕቃውንም ስጦታ መዝኜ ሰጠኋቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ንጉሡ፣ አማካሪዎቹ፣ ሹሞቹና በዚያ የነበሩ እስራኤል ሁሉ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን ብር፣ ወርቅና ዕቃ ሁሉ መዝኜ ሰጠኋቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ከዚህ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ፥ አማካሪዎቹ፥ ባለሟሎቹና በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን ለቤተ መቅደስ መገልገያ ይሆን ዘንድ የሰጡትን ብር፥ ወርቅና ሌሎቹንም ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ በሚዛን መዝኜ ለእነዚህ ካህናት አስረከብኳቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ንጉሡና አማካሪዎቹ፥ አለቆቹም፥ በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ ያቀረቡትን፥ ለአምላካችን ቤት የቀረበውን ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃውንም መዝኜ ሰጠኋቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ንጉሡና አማካሪዎቹ፥ አለቆቹና በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ ያቀረቡትን ለአምላካችን ቤት የቀረበውን ብሩንና ወርቁን ዕቃውንም መዝኜ ሰጠኋቸው። See the chapter |