Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕዝራ 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እስከ መቶ መክሊት ብር፥ እስከ መቶ የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት፥ ጨውም የሚፈልገውን ያህል ሳትጽፉ ስጡት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እስከ አንድ መቶ መክሊት ብር፣ እስከ አንድ መቶ ቆሮስ ስንዴ፣ እስከ አንድ መቶ ባዶስ መስፈሪያ ወይን ጠጅ፣ እስከ አንድ መቶ ባዶስ የወይራ ዘይትና የሚፈለገውን ያህል ጨው ስጡት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እስከ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብር፥ እስከ ዐሥር ሺህ ኪሎ ስንዴ፥ እስከ ሁለት ሺህ ሊትር የወይን ጠጅ፥ እስከ ሁለት ሺህ ሊትር የወይራ ዘይትና የሚያስፈልገውንም ያኽል ጨው ስጡት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እስከ መቶ መክ​ሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ የወ​ይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እስከ መቶ መክሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶ የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን ስጡ።

See the chapter Copy




ዕዝራ 7:22
5 Cross References  

የዘይቱም ደንብ፥ ከእያንዳንዱ የቆሮስ መስፈሪያ የባዶስን አንድ አሥረኛ ክፍል ትሰጣላችሁ፤ ዐሥር የባዶስ መስፈሪያ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ነውና።


የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።


እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ለምትገኙ ገንዘብ ያዦች ሁሉ፦ የሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤


በንጉሡና በልጆቹ መንግሥት ላይ ቁጣ እንዳይሆን፥ የሰማያት አምላክ የሚያዘው ሁሉ ልክ እንዳዘዘው ለሰማያት አምላክ ቤት ይደረግ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements