Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕዝራ 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አስቀምጠው የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ’” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ቀጥሎም፣ ‘እነዚህን ዕቃዎች ይዘህ ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው፤ የእግዚአብሔር ቤት ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንደ ገና ይሠራ’ አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ይኸው አገረ ገዢው ሼሽባጻር እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት መልሶ በማምጣት በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖር ዘንድ፥ እንዲሁም ቤተ መቅደሱ ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይ ተመልሶ እንዲሠራ ያደርግ ዘንድ፥ ንጉሠ ነገሥቱ ቂሮስ አዞታል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው መቅ​ደስ በቦ​ታው አኑ​ረው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠራ’ አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 “ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አኑረው፤ የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ” አለው።

See the chapter Copy




ዕዝራ 5:15
5 Cross References  

በንጉሡ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ በኢየሩሳሌም ስላለው ስለ እግዚአብሔር ቤት እንዲህ ብሎ አዘዘ፥ መሥዋዕት የሚሠዋበት ቦታ፥ ይህ ቤት ይሠራ፥ በጽኑም ይመሥረት፤ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ ስፋቱም ስድሳ ክንድ ይሁን።


በምድሩ ካሉት ሕዝቦች የተነሣ ፈርተው ነበርና፥ መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት በጠዋትና በማታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ።


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤


ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያመጣውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሼሽባጻር ለተባለው፥ ገዢ ላደረገው ሰጠው፤


በዚያን ጊዜ ይህ ሼሽባጻር መጣ፥ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ ነው አላለቀምም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements