ዕዝራ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ነገር ግን አባቶቻችን የሰማያትን አምላክ ስላስቆጡት በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ነገር ግን አባቶቻችን የሰማይን አምላክ አስቈጥተውት ስለ ነበር፣ ለባቢሎኑ ንጉሥ ለከለዳዊው ናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤተ መቅደስ አፈራርሶ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ይህን የሰማይ አምላክ በማስቈጣታቸው ምክንያት በከለዳውያን ሥርወ መንግሥት የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነው በናቡከደነፆር ጦር እንዲሸነፉ አደረገ፤ ቤተ መቅደሱ ፈራረሰ፤ ሕዝቡም ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አባቶቻችንም የሰማይን አምላክ ከአስቈጡ በኋላ በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አባቶቻችንም የሰማይን አምላክ ካስቈጡ በኋላ በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ። See the chapter |