ዕዝራ 4:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 የንጉሡም የአርጤክስስ ደብዳቤ ግልባጭ በሬሑምና በጸሐፊው በሺምሻይ በተባባሪዎቻቸውም ፊት በተነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ ሄዱ፤ በግድና በኃይልም አስተዉአቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 የንጉሡ የአርጤክስስ ደብዳቤ ቅጅ በሬሁም፣ በጸሓፊው በሲምሳይና በተባባሪዎቻቸው ፊት እንደ ተነበበ፣ ወዲያውኑ በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት አይሁድ ሄደው ሥራውን እንዲያቆሙ አስገደዷቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ንጉሠ ነገሥቱ አርጤክስስ የላከው የመልስ ደብዳቤም መጥቶ ለረሑም፥ ለሺምሻይና ለተባባሪዎቻቸው ሁሉ እንደ ተነበበላቸው፥ ወዲያውኑ ወደ ኢየሩሳሌም ገሥግሠው በመምጣት ሕዝቡን በማስገደድ የኢየሩሳሌምን ከተማ እንደገና ከመሥራት አገዱአቸው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 የንጉሡም የአርተሰስታ መልእክተኛ በደረሰ ጊዜ በአዛዡ በሬሁምና በጸሓፊው በሲምሳይ፥ በተባባሪዎቻቸውም ፊት መልእክቱን ባነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ በፈረስ ሄዱ፤ በኀይልም አስተዉአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 የንጉሡም የአርጤክስስ ደብዳቤ ግልባጭ በሬሁምና በጸሐፊው በሲምሳይ በተባባሪዎቻቸውም ፊት በተነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ ሄዱ፤ በግድና በኃይልም አስተዉአቸው። See the chapter |