Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕዝራ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ አሁን ሁላችን የቤተ መንግሥቱን ጨው እንበላለንና፥ የንጉሡ አለመከበር ማየት አይገባንምና ስለዚህ ልከን ለንጉሡ አስታወቅን፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አሁንም እኛ ስለ ቤተ መንግሥቱ ስለሚገደን፣ የንጉሡም ክብር ሲነካ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው፣ ይህ ነገር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ እንዲሆን ይህን መልእክት ልከናል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኛም የቤተ መንግሥቱ ጥቅም ተካፋዮች በመሆናችን አለመከበርዎን እያየን ዝም ማለትን ስላልወደድን ይህን ሐሳብ እናቀርባለን፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ንጉ​ሡ​ንም ሲያ​ቃ​ል​ሉት ማየት አይ​ገ​ባ​ን​ምና ስለ​ዚህ ልከን ለን​ጉሡ አስ​ታ​ው​ቀ​ናል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የንጉሡንም ጨው እንበላለንና፥ ንጉሡንም ሲያቃልሉት ማየት አይገባንምና ስለዚህ ልከን ለንጉሡ አስታውቀናል፤

See the chapter Copy




ዕዝራ 4:14
5 Cross References  

ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።


አሁንም ይህች ከተማ ከተገነባች፥ የቅጥሮቿም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንዳይሰጡ፥ ንጉሡንም እንደሚጎዳ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።


በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዓመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጐዳች፥ ከጥንቱም ሽፍትነት በእርሷ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፥ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements