Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕዝራ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ተነሥ ይህም ነገር የአንተ ሥራ ነውና፥ እኛም ከአንተ ጋር እንሆናለን፤ በርታ፥ አድርገውም።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዕዝራ፣ ነገሩ በእጅህ ነው፤ ተነሥ! እኛም እንደግፍሃለን፤ በርትተህም አድርገው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይህንንም ሁሉ ለማስፈጸም ኀላፊነቱ የአንተ ስለ ሆነ ተነሥ፤ እኛም እንደግፍሃለን፤ አይዞህ በርታ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ይህም ነገር ለአ​ንተ ይገ​ባ​ልና፥ እኛም ከአ​ንተ ጋር ነንና ተነሣ፤ በርታ፤ አድ​ር​ገ​ውም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ይህም ነገር ለአንተ ይገባልና፥ እኛም ከአንተ ጋር ነንና ተነሣ! አይዞህ፤ አድርገው።”

See the chapter Copy




ዕዝራ 10:4
14 Cross References  

አሁንም፥ እነሆ፥ ጌታ ለመቅደስ የሚሆን ቤትን እንድትሠራ መርጦሃልና በርትተህ በቈራጥነት ፈጽመው።”


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተሳሰብ፤


አሁንም አምላካችሁን ጌታን ለመሻት ልባችሁንና ነፍሳችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ ስጡ፤ ለጌታም ስም ወደሚሠራው ቤት የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን ንዋየ ቅድሳት ለማምጣት ተነሥታችሁ የጌታን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።”


የሚሠሩበት ወርቅና ብር ናስና ብረት ቍጥር የለውም፤ ተነሥተህ ሥራ፥ ጌታም ከአንተ ጋር ይሁን።”


ይህም ቤቱን ለአገልጋዮቹ ትቶ፥ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፥ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል።


እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥራ በብልሃትና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል።”


ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹን፥ ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልንም ሁሉ እንደዚህ ቃል እንዲያደርጉ አስማላቸው፥ እነርሱም ማሉ።


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements