ሕዝቅኤል 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 በምድር የምትኖር ሆይ፥ ፍጻሜህ ወደ አንተ መጥቷል፥ ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሽብር ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እናንተ በምድሪቱ የምትኖሩ ሆይ፤ የጥፋት ፍርድ መጥቶባችኋል፤ ጊዜው ደርሷል፤ በተራሮች ላይ እልልታ ሳይሆን ሽብር የሚሰማበት ቀን ቀርቧል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 በምድሪቱ የምትኖሩ ሕዝብ ሁሉ የመጥፊያችሁ ጊዜ ደርሶአል፤ ጊዜው ደርሶአል፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ እርሱም የሁከት ቀን ነው እንጂ በከፍተኛ ቦታዎች የመፈንጠዣ ቀን አይደለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በሀገር የምትኖር ሆይ! ስብራትህ ጊዜው ደረሰ፤ ቀኑም ቀረበ፤ የሽብር ቀን ነው እንጂ የተራራ ላይ ዕልልታ አይደለም፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በምድር የምትቀመጥ ሆይ፥ ተራህ ደርሶአል፥ ጊዜ መጥቶአል፥ ቀን ቀርቦአል፥ የሽብር ቀን ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም። See the chapter |