Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሕዝቅኤል 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለራስህ ጡብን ውሰድ፥ በፊትህም አኑራት፥ በላይዋ ላይም የኢየሩሳሌምን ሥዕል ሳልባት፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “አንተ፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ አንድ የሸክላ ጡብ ወስደህ ከፊት ለፊትህ አስቀምጥ፤ የኢየሩሳሌምን ከተማ ካርታ ሥራበት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አኑር፤ በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ የሚያመለክት ካርታ ንደፍበት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጡብን ወስ​ደህ በፊ​ትህ አኑ​ራት፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከተማ ሥዕል ሣል​ባት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጡብን ወስደህ በፊትህ አኑራት የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት፥

See the chapter Copy




ሕዝቅኤል 4:1
17 Cross References  

እንዲህም ይላል፦ “እኔ ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


እኔም ጌታ፥ ከግብጽ ጀምሬ አምላክህ ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀን እንደገና በድንኳን እንድትኖር አደርግሃለሁ።


ይህች ከተማ ከሠሩአት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቁጣዬንና መዓቴን አነሣሥታለችና ከፊቴ አስወግዳታለሁ፤


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዛፎችዋን ቁረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፤ በመካከልዋ ያለው ነገር ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣበትን ሁለት መንገዶችን አድርግ፥ ሁለቱም ከአንዲት ምድር ይውጡ፥ ምልክትም አድርግ፥ በከተማይቱ መንገድ ራስ ላይ አድርገው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements