Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሕዝቅኤል 38:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የማጎግ ምድር፥ በሮሽ፥ በሜሼኽና በቱባል ላይ አለቃ ወደ ሆነው ወደ ጎግ ፊትህን አቅና፥ ትንቢትም ተናገርበት፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን በማጎግ ምድር በሚገኘው፣ በሜሼኽና በቶቤል ዋና አለቃ በጎግ ላይ አድርግ፤ በርሱ ላይ ትንቢት ተናገር፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! በማጎግ ምድር የሚገኙት የሜሼክና የቱባል ሕዝቦች ገዢ የሆነውን ጎግን በመቃወም ትንቢት ተናገርበት፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን በጎግ ላይና በማ​ጎግ ምድር ላይ፥ በሮስ በሞ​ሳ​ሕና በቶ​ቤል አለቃ ላይ አቅ​ና​በት፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥

See the chapter Copy




ሕዝቅኤል 38:2
18 Cross References  

አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ አሁንም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥


እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮሽ፥ የሜሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።


ያቫን፥ ቱባልና ሜሼክ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር፤ ዕቃሽን በሰዎች ነፍስና በናስ ዕቃ ይለውጡ ነበር።


የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክ እና ቲራስ ናቸው።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርባቸው፤


እርሱም፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ ከአንተ ጋር እንድነጋገር በእግርህ ቁም” አለኝ።


በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል።


በማጎግ እና ያለ ስጋት በደሴቶች በሚቀመጡት ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ሜሼክና ቱባል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሰይፍ ተገድለዋል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ አሞን ልጆች አድርገህ ትንቢት ተናገርባቸው።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና ወደ ደቡብም ተናገር በደቡብም ባለው ዱር ላይ ትንቢት ተናገር፤


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።


መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ጎግንም እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ እስራኤል በሰላም በተቀመጠ ጊዜ በዚያ ቀን አንተ አታውቀውምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements